የአዲስ አበባ ሆቴል ባለቤቶች ማህበር የቦርድ አባላትን መረጠ
Mar 18, 2025
የአዲስ አበባ ሆቴል ባለቤቶች ማህበር የቦርድ አባላትን መረጠ
የአዲስ አበባ ሆቴል ባለቤቶች ማህር የካቲት 22/2017 ዓ.ም በግዮን ሆቴል ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ የቦርድ አባላትን መርጧል፡፡
ማህበሩ ባለፈው ዓመት የተሰሩ ስራዎች በማህበሩ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ አስቴር ሰለሞን እንዲሁም የኦዲት ሪፖርት በአቶ ታምብዞት ምንውዬ ቀርቦ ጸድቋል።
በማህበሩ መተዳደሪያ ደምብ መሰረት ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ ቦርድ አባላትን በአዲስ ተክቷል፡፡
በዚህ መሰረት ከነባር
1. ወ/ሮ አስቴር ሰለሞን
2. አቶ የሺጥላ አሰፋ
3. ወ/ሮ እየሩሳለም እንዳለ እና
4. ወ/ሮ ብሌን አያና
በቀጣይነት ማህበሩን እንዲመሩ የተወሰነ ሲሆን
አዲስ የተመረጡት
1. አቶ ዮናኤል ታዲዮስ
2. ወ/ሮ ሰናይት በዙ
3. ደ/ር ምህረት ገ/ማሪያም
እንዲሁም በተጠባባቂነት
1. አቶ ናሆም አለማየሁ
2. አቶ ሀብታሙ ዮሴፍ
የተመረጡ ሲሆን በቁርጠኝነትና በቅንነት ማህበሩን እንደሚያገለግሉ ቃል ገብተዋል፡፡
1250 Eye Street, N.W., Suite 1100
Washington, D.C. 20005
Ethiopian Tourism Transformation Council
Ethiopian Industry Transformation Member
Entoto poly Technic College Technical Advisory Board